900 ሺህ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ 62 ሚሊየን ዶላር ያሥፈልጋል ተባለ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በቀጣይ ስድስት ወራት 900 ሺህ ያህል ተፈናቃዮችን ለመደገፍ 62 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ፡፡
የሥደተኞችን ሕይወት ለመታደግ የተጠየቀው የገንዘብ ድጋፍ በአስቸኳይ እንደሚያስፈልግ አሳስቧል፡፡
አሁን ላይ በሶማሌ ክልል ቦክ አካባቢ 100 ሺህ ለሚደርሱ ተፈናቃዮች ድጋፍ እያቀረቡ መሆኑንም ድርጅቱ ጠቁሟል፡፡