የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከስሎቬኒያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ታንያ ፋዬን ጋር ተወያዩ

By Mekoya Hailemariam

April 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስሎቬንያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ታንያ ፋዬን ጋር ተወያዩ።

በዚህም ወቅት፥ በኢትዮጵያና በስሎቬኒያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በኩል ያስታወቁት።

በስሎቬኒያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ታንያ ፋዬን የተመራው የሀገሪቱ ልዑክ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ከቀናት በፊት ነበር ወደ አዲስ አበባ የመጣው።

በቆይታውም የተለያዩ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችን በማግኘት በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ መክሯል።