Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ መጪዎቹን የፋሲካ እና የዒድ አልፈጥር በዓላት ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርተዋል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በመገኘት ለተቸገሩ ወገኖች እና አቅመ ደካሞች ማዕድ ያጋሩት ፕሬዚዳንቷ ወቅቱ የክርስትና እና እስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የፆም እና የጸሎት ወቅት መሆኑን በማንሣት መረዳዳት እና መደጋገፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደምም በተለይም በወረዳው የሚገኙ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ታዳጊዎችን ለመደገፍ ጥረት መደረጉን ገልጸው በዚህ ወቅት መረዳዳት ግዴታ ጭምር ነው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሞላ ንጉሥ ÷ ከ10 ሺህ በላይ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በዚህ ዓመት ብቻ ጊዜያዊ እና ዘለቂ የማዕድ ማጋራት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.