Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በዋናነትም የክልሉን የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላትን ለማቋቋም እና አስተዳደራቸውን ለመወሰን የወጣ ረቂቅ ደንብ እና ለኢንቨስተሮች የመሬት ምደባ ላይ በሰፊው ተወያይቶ አፅድቋል።

በውይይቱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፥ ወጣቱ ሀገር ተረካቢ፣ መልካም ስብእና ያለው እና ምከንያታዊ የሆነ ወጣት ለመፍጠር የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከል ማቋቋሚያ ደንብ መውጣቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቅሰዋል።

በኢንቨስትመንትን ከማጠናከር እና ከማስፋፋት አንፃር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ማጠናከር ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወስደው ወደ ልማት የገቡ ባለሀብቶችን መደገፍ እና ማበረታታት እንደሚገባ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ፍቃድ ወስደው በማያለሙ ባለሀብቶች ላይ የሚደረገው የክትትል እና የቁጥጥር ሥራው ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.