Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከህንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከህንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንከር ጋር ተወያዩ።

በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ ስለፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አተገባበር፣ ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች እየተደረገ ስላለው ሰብአዊ ድጋፍና መሰረታዊ አገልግሎቶችን የማስጀመር ሂደት በተመለከተ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

በተጨማሪም ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ገለጻ ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም አቶ ደመቀ ህንድ ከሰሜኑ ግጭት እና ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ያሳየችውን ድጋፍ አድንቀዋል።

አቶ ደመቀ አያይዘውም እንደ ህንድ ያሉ የኢትዮጵያ አጋሮች በአዳጊ ሀገራት የዕዳ ማሻሻያ ጥያቄ ላይ አወንታዊ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባቸዋል ብለዋል።

የህንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንከር በበኩላቸው፥ በኮቪድ ምክንያት ሳይካሄድ የቀረው የአፍሪካ – ህንድ ስብሰባ የአዳጊ ሀገራትን ፍላጎት ባስጠበቀ መልኩ በተያዘው አመት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.