Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ በመንገድ መሰረተ ልማት የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ እየተሰራ ነው -አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በክልሉ የተሰሩ የመንገድ መሰረተ ልማትን ጎብኝተዋል፡፡

አቶ ደስታ በጉብኝታቸው÷በሁላ እና በቦና ወረዳ እየተሰራ የሚገኘውን የመንገድ መሰረተ ልማት ተመልክተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንደገለፁት÷የክልሉ መንግስት በመንገድ መሰረተ ልማት የሚነሳውን ጥያቄ በቁርጠኝነት ለመመለስ እየተሰራ ነው።

ርዕሰ መስተዳድሩ የተጀመሩ መንገዶች ያሉበትን ደረጃም የገመገሙ ሲሆን÷ መንገዶቹ በፍጥነት ተጠናቀው ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ መመሪያ ሰጥተዋል።

በጉብኝቱ በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.