Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ከ353 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመንገድ ሥራ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው በጀት ዓመት በአፋር ክልል ከ353 ሚሊየን 331 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ እየተከናወነ ነው።

ለመንገድ ግንባታ ስራው 257 ሚሊየን እና ለጥገና 96 ሚሊየን 331 ሺህ 880 ብር መመደቡን የአፋር ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ የመንገድ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ከድር መሀመድ (ኢ/ር) ተናግረዋል፡፡

የክልሉ የመንገድ ሽፋን 3 ሺህ 185 ኪሎ ሜትር መሆኑን ጠቁመው፥ በ2015 ዓ.ም 3 ሺህ 400 ኪሎ ሜትር ለማድረስ መታቀዱን ገልፀዋል።

በዚህ ዓመት ከ119 ኪሎ ሜትር በላይ አዲስ መንገድ ለመክፈት ታቅዶ ከ28 ኪሎ ሜትር በላይ መከናወኑን አስረድተዋል።

6 ኪሎ ሜትር ደረጃውን የጠበቀ መንገድ ለመገንባት ቢታቀድም በፀጥታና ሌሎች ምክንያቶች አለመፈፀሙን አንስተዋል።

የነበረውን የፀጥታ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ 247 ኪሎ ሜትር የመንገድ ከፈታ ሥራ መከናወኑንም አመላክተዋል።

በ2015 ዓ.ም ሁለት ድልድዮች ለመገንባት ታቅዶ አንዱ መጠናቀቁንና የሁለተኛው ድልድይ ግንባታ አፈጻጸም 20 በመቶ መድረሱን አብራርተዋል።

በተጨማሪም 412 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና ለማከናወን ታቅዶ እስካሁን የ224 ኪሎ ሜትር ጥገና መፈፀሙን ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለፁት።

በነበረው ግጭት ምክንያት የተጎዱ መንገዶችን በመጠገን አብዛኛዎቹን ወደ አገልግሎት መመለስ መቻሉንም አረጋግጠዋል።

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.