የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎችን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው

By Tamrat Bishaw

April 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ተጎራባች አካባቢዎችን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ውይይት በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው።

ውይይቱን እየመሩ የሚገኙት የአሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ናቸው፡፡

በውይይቱ ላይ የሁለቱም ክልሎች ከፍተኛ አመራሮችና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ይህም የሁለቱን ክልሎች ሁለንተናዊ ግንኙነት አጠናክሮ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር የሚያግዝ መሆኑ ነው የተመለከተው፡፡