የሀገር ውስጥ ዜና

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

By Tamrat Bishaw

April 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።

ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ቆይታ ይኖራቸዋል።