ስፓርት

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተለያዩ

By Tamrat Bishaw

April 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝነት በጋራ ስምምነት መለያየታቸው ተገለጸ፡፡

ተሰናባቹ አሰልጣኝ ከመስከረም 2013 ዓ.ም ጀምረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት መርተዋል፡፡

ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው÷ አሰልጣኝ ውበቱ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ የአሰልጣኙን መልቀቂያ በመቀበሉ በጋራ ስምምነት ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለነበራቸው ቆይታ ምስጋና አቅርቧል፡፡