Fana: At a Speed of Life!

ለክትባት ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ 30 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የክትባት ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት የሚያስችል 30 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ፡፡

በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለዚሁ ዓላማ የሚገነባው የክትባት ፋብሪካ ባለሀብቶችን የሚያሳትፍ መሆኑ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ በመድኃኒት አምራች ዘርፍ ላይ ለመሰማራት ከሚፈልጉ 20 ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር ጤና ሚኒስቴር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፋብሪካውን የገነባው ‘አፍሪኪዩር ፋርማሲቲካልስ’ እና በደብረ ብርሃን ኩባንያውን የተከለው ‘ትረስት ፋርማሲዩቲካል’ የተሰኙ አምራች ኩባንያዎች በቅርቡ ወደ ምርት እንደሚገቡም ተጠቁሟል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ጋር ክትባቶቹን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማምረት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ በቅርቡ በዝርዝር መወያየታቸው ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.