ዓለምአቀፋዊ ዜና

የጃፖኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ከተሞከረባቸው ጥቃት መትረፋቸው ተሰማ

By Amele Demsew

April 15, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ከተሞከረባቸው ጥቃት መትረፋቸው ተሰማ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል በምትገኘው ዋካያማ ከተማ ንግግር እያደረጉ በነበረበት ወቅት “የጭስ ቦምብ” እንደተወረወረባቸው የሀገሪቱን መገናኛ ብዙሃን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል።

በወቅቱ በአካባቢው ከፍተኛ ፍንዳታ ቢሰማም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አለመጎዳታቸውንም ነው ዘገባው ያመላከተው።

ፖሊስም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ዩጂ ኪሙራ የተባለ የ24 አመት ወጣት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

ባለፈው አመት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ የነበሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በአንድ አጥቂ በተተኮሰ ጥይት ለህልፈት መዳረጋቸው ይታወሳል።