የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር የትንሳኤ በዓል ስጦታ አበረከቱ

By Tibebu Kebede

April 17, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር በመሆን በተለያዩ አካባቢዎች የትንሳኤ በዓል ስጦታዎችን አበርክተዋል።

በዚህም መነን ትምህርት ቤት ወደሚገኘው የህክምና ባለሙያዎች ማቆያ በመሄድ የተለያዩ ስጦታዎችን ለህክምና ባለሙያዎቹ አስረክበዋል።

በተጨማሪም ፍልውሀ አካባቢ ለሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ለበዓል የሚሆኑ የተለያዩ ስጦታዎች ማበርከታቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅቱ ትብብርን የሚጠይቅ በመሆኑ ህብረተሰቡ እርስ በእርሱ እንዲረዳዳና ያለውን እንዲካፈል ጥሪ መቅረቡ ይታወቃል።