የሀገር ውስጥ ዜና

የፋሲካ በዓል ተከበረ

By ዮሐንስ ደርበው

April 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የፋሲካ በዓል ተከበረ፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ለሰው ልጅ ደኅንነት፣ ሰላም የተገኘበት መሆኑን የሃይማኖት አባቶች ገልጸዋል፡፡

ስለሆነም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የተገኘውን ሰላም፣ ክርስቲያኑ ምዕመን በጎ ተግባራትን በማከናወን ሊተገብር ይገባል ነው ያሉት፡፡

ክርስቲያኑ ምዕመን ለሀገር ሰላምና፣ አንድነት መረጋገጥ ተግቶ እንዲሠራም ነው የሃይማኖት አባቶች መልዕክት ያስተላለፉት፡፡

በዓሉን ከተቸገሩ ወገኖች ጋር አብሮ ማሳለፍ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!