የቻይና ኢኮኖሚ ከ28 ዓመት በኋላ ዝቅተኛ እድገት አስመዘገበ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ኢኮኖሚ በፈረንጆቹ 2020 የመጀመሪያ ሩብ አመት ዝቅተኛ የተባለውን እድገት ማስመዝገቡ ተነገረ።
አሁን የተመዘገበው እድገት ከ28 አመታት በኋላ ዝቅተኛው ነው ተብሏል።
በአዲሱ የፈረንጆቹ አመት የመጀመሪያ ሶስት ወራትም የሃገሪቱ ኢኮኖሚ 6 ነጥብ 8 መቀነሱ ተነግሯል።
ለዚህ ደግሞ መነሻውን ውሃን ከተማ ያደረገው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት መሆኑ ነው የተነገረው።
አሁን ላይ በቫይረሱ ሳቢያ ፋብሪካዎች መዘጋታቸውና የንግድ እንቅስቃሴዎች መቆማቸው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳርፏል።
ከዚህ ባለፈም የሃገሪቱ የስራ አጥ ቁጥር ጭማሪ አሳይቷል ነው የተባለው።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision