አምባሳደሮች ለፋሲካ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች እና አምባሳደሮች ለክርስትና እምነት ተከታዮች ለፋሲካ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞታቸውን ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን “የፋሲካ በዓል የአዲስ ሕይወትና አዲስ ተስፋ መግለጫ ነው” ሲሉ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።
“በዚህ ብሩህ በዓል ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቼና እህቶቼ ሁሉ ሰላምን ለመመኘት እወዳለሁ” ብለዋል።
“ሰላም የሁሉ ነገር መሰረት ነው” ያሉት አምባሳደሩ÷ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሰላም እንዲሆን ምኞቴ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የፋሲካ በዓል የሰላም፣ የደስታና ብልጽግና እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በተመሳሳይ ÷ በኢትዮጵያ የእስራኤል፣ ብሪታኒያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ዴንማርክ፣ ኢራን፣ ሜክሲኮ፣ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ፓኪስታን፣ ስሪላንካ እና ኦስትሪያ ኤምባሲዎችና አምባሳደሮች የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የደስታና የሐሴት እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል ዘግቧል፡፡