ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ለፋሲካ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ለፋሲካ በዓል የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ።
በመልዕክታቸውም÷ “ለሀገራችን ክርስቲያኖች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በደኅና አደረሰን! የኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና ሞት እንዳለ ሆኖ ምኅረት፣ የዘለዓለም ሕይወት፣ የመንፈስ ጥንካሬና ጽናት… የተገኘው በትንሳኤው ነው” ብለዋል።
ችግሮችን አስቀድሞ መከላከል ላይ እንበርታ ሲሉም ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መልዕክት ገልጸዋል፡፡