በአዲስ አበባ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ ሊንቀሳቀሱ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የቤት ተሽከርካሪዎች (ኮድ-2) በፈረቃ ሊንቀሳቀሱ መሆኑ ተገለጸ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም በሚኒስትሮች ኮሚቴ የወጣ የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ ላይ መግለጫ ተሰጥቷል።
በመግለጫው ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ኮድ 2 የሆኑ የቤት ተሽከርካሪዎች በሰሌዳ ቁጥራቸው ሙሉና ጎዶሎነት በፈረቃ እንደሚንቀሳቀሱ ተገልጿል።
በዚህም የሰሌዳቸው የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ ወይም ዜሮ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ዛሬ ዓርብ የሚንቀሳቀሱ ሲሆን፥ የሰሌዳ ቁጥራቸው መጨረሻ ጎዶሎ የሆነ ተሽከርካሪዎች ደግሞ ነገ ቅዳሜ ይንቀሳቀሳሉ ተብሏል።
ፈረቃው ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ወራት በየቀኑ በተሽከርካሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥር መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
ክልሎችም እንደራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ መመሪያ አውጥተው እንደሚተገብሩት ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በመግለጫው ላይ የከተማ ታክሲ አገልግሎት በሚሰጡም ሆነ በሃገር አቋራጭ አውቶብሶች ላይ የወጣው መመሪያ በአግባቡ እንደሚተገበር ተነስቷል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision