Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከሱዳን አቻቸው ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር አሊ ኢል ሳዲግ አሊ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ ለሱዳን ህዝብ ያላትን አጋርነት እንዲሁም በተከሰተው ግጭት በሞቱ ዜጎች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡

የሱዳን ህዝብ በተለይም በተቀደሰው ረመዳን ወር የተከሰተውን ግጭት በማርገብ ወደ ቀድመ ሰላም እንደሚመለስ ያላቸውን እምነት መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.