Fana: At a Speed of Life!

በዓሉ እንቅስቃሴያችንን ገድበን የምናከብረው መሆን አለበት – ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰዎች የፋሲካ በዓልን እንቅስቃሴያቸውን በመገደብ ሊያከብሩ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገለፁ።

የጤና ሚኒስትሯ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም “በዓሉ እርስ በእርስ ማዕድ የምንቋደስበት፣ፍቅርን እና መተሳሰብን የምንገልፅበት ቢሆንም አሁን እንቀድሞ ጎረቤት፣ ዘመድ አዝማድ ተጠራርቶ የሚከበረው ሳይሆን አብረን ከምንኖራቸው የቤተሰብ አባላቶች ጋር ብቻ ሆነን የምናከብረው መሆን ይኖርበታል” ብለዋል።

ፍቅራችንንም አንዱ ለአንዱ በመጠንቀቅ የምንገልፅበት መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ወደ መገበያያ ስፍራዎችም ሲኬድ አካላዊ ርቀትን ጠብቀን እና የአፍ መሸፈኛዎችን በመጠቀም መሆን እንደሚገባው ነው ያሳሰቡት።

የእንሰሳት እርድ በሚካሄድበት ጊዜም በጥንቃቄ ሊሆን ይገባል ያሉት ዶ/ር ሊያ፥ ምግብንም አብስሎ መመገብ ይገባል ነው ያሉት።

እራሳችንን መገደባችን፣ መታግሳችን እና ዛሬ የምንወስዳቸው እርምጃዎች ለወደፊት በጥሩ ሁኔታ ማክበር እንድንችል ወሳኝ እርምጃዎች መሆናቸውንም አንስተዋል።

በመጨረሻም ይህንን በዓል ወረርሽኙን ለመከላከል በተለያዩ ቦታዎች በስራ ላይ የሚያሳልፉ የህክምና ባለሙያዎች እና ሌሎችም እያበረከቱ ላሉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.