የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከሀንጋሪ የውጭ ጉዳይና የንግድ ሚኒስትር ጋር መከሩ

By Feven Bishaw

April 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሀንጋሪ የውጭ ጉዳይና የንግድ ሚኒስትር ፒተር ሲያርቶ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የሚገኙት ፒተር ሲያርቶ ከትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር ሁለቱ ሀገራት በከፍተኛ ትምህርት በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ይታወቃል።

ኢትዮጵያና ሀንጋሪ 60 ዓመት ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።