የሀገር ውስጥ ዜና

በዓሉን ስናከብር ደም በመለገስና ያለንን በማካፈል እንዲሆን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ

By Feven Bishaw

April 17, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የትንሳኤ በዓልን ስናከብር በድንገተኛ የህክምና ችግር ውስጥ ላሉ ወገኖቻችን የሚሆን ደም በመለገስና ካለን በማካፈል መሆን እንዳለበት የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ።

ወይዘሮ አዳነች በብሔራዊ ደም ባንክ በመገኘትም ደም ለግሰዋል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ደም መለገስን ጨምሮ አለኝ የሚለውን ማንኛውንም ነገር ለወገኖቹ በማካፈል በዓሉን እንዲያሳልፍም ጥሪ አቅርበዋል።