Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሲዳሚኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት “እንኳን ለሲዳማ አዲስ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሰን” ብለዋል።

ፊቼ ጫምባላላ የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ከመሆን አልፎ የዓለም ቅርስ ሆኖ ከተመዘገበ ዓመታትን አስቆጥሯል ነው ያሉት።

ይህንን ልዩ በዓል በመጠበቅ ለዚህ ትውልድ ላበቁ አባቶቻችን ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል በመልዕክታቸው።

የዘንድሮውን በዓል የምናከብረው የበዓሉ ምልክት የሆነው የሰላም ችቦ በሀገራችን ውስጥ መብራት በጀመረበት ወቅት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ሰላም፣ በረከትና ተስፋ በፍቼ በዓል ውስጥ የሚታዩ ምልክቶች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አንስተዋል።

አክለውም፥ “እነዚህ ምልክቶች ለሕዝባችን ሰላምን አውርደው፣ ድህነትን ቀብረው ወደ በረከትና ብልፅግና ለመጓዝ የዕቅዳችን አካል ናቸው” ነው ያሉት።

ስለሆነም “የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን እና ወጣቶች፥ የመንግስትን የሰላም፣ የበረከትና የብልፅግና መንገድ ከፍቼ በዓል ጋር ያለውን ዝምድና ጠንቅቆ በማወቅ ሀገሪቱን ከችግር በማላቀቅና የበለፀገች ሀገር ለትውልዱ ለማስተላለፍ በጀመርነው መንገድ ከጎናችን እንድትቆሙ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.