የሀገር ውስጥ ዜና

የገንዘብ ሚኒስቴር እና የፈረንሳይ ኤምባሲ የኢኮኖሚ ኮሚቴዎች የውይይት መድረክ ተጀመረ

By Mikias Ayele

April 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሶስተኛው የገንዘብ ሚኒስቴር እና የፈረንሳይ ኤምባሲ የኢኮኖሚ ኮሚቴዎች ውይይት በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ የኢትዮጵያ እና የፈረንሳይ የፋይናንስ ባለሙያዎች፣ ባለስልጣናት እና የፈረንሳይ ኩባንያ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው፡፡

በውይይት መድረኩ የፈረንሳይ ኩባንዎች የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ሊደገፉ በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በታዳሽ ሀይል ዘርፍ ያሉ የኢንቨስትመንት ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎቻቸውን በተመለከት ውይይት ይደረጋል፡፡

8ከሰዓት በሚኖረው ውይይት ደግሞ የተለያዩ ኩባንያዎች ሃላፊዎች ተጋብዘው ተሞክሮዎቻቸውን በመድረኩ ያቀርባሉ መባሉን ከፈረንሳይ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡