Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦችን ተፈጻሚ ለማድረግ ያላት ቁርጠኝነት ተደነቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦችን ተፈጻሚ ለማድረግ ያላት ቁርጠኝነት የሚደቅ ነው ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሬዚደንስና የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ ገለጹ፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር  ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሬዚደንስና የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ ካትሪን ሱዚ ጋር ተወያይዋል፡፡

በ2030 ለማሳካት የተቀመጡ አጀንዳዎችንና የዘላቂ የልማት ግቦችን አፈጻጸም በሚገመግመው ዓለም አቀፉ የዘላቂ ግቦች ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ተሳትፎ በተመለከተ ፍጹም (ዶ/ር) በውይይታቸው ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡

በዓለም አቀፍና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተፈጠሩ የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም የልማት ግቦችን ለማሳካት  ውጤት ያመጡ ተግባራት ተከናውነዋል ማለታቸውን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በጉባዔው ላይ በጥሩ ጎን ሊቀርቡ የሚገባቸው ውጤታማ ተሞክሮዎች አሉን ያሉት ሚኒስትሯ÷ ለዚህም በቂ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ነው ያረጋገጡት፡፡

ካትሪን ሱዚ በበኩላቸው÷ ምንም እንኳን በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ብትሆንም ኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦችን ተፈጻሚ ለማድረግ ያላት ቁርጠኝነትና የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

ሀገሪቱ በመልሶ ማቋቋምና በሰብዓዊ ድጋፍ ላይ በርካታ ተግባራትን እያከናወነች ነው ያሉት አስተባባሪዋ÷ ለዚህም  አጋር አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ነው የጠየቁት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.