አቶ ኦርዲን በድሪ በሐረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡
አቶ ኦርዲን በክልሉ ሐኪም ወረዳ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መጎብኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀዳማዊ እመቤት ጽሕፈት ቤት የሚሰራው የሐረር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ መሠረተ ልማቶች፣ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች እና የአስፋልት መንገድ ግንባታዎች ከተጎበኙት ፕሮጀክቶች መካከል ይገኙበታል፡፡
በተጨማሪም በክልሉ ባሕል ማዕከል ቅጥር ግቢ እየተገነባ የሚገኘው የሐረሪ እና የኦሮሞ ባሕል ቤቶች፣ የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ሥራዎች እንዲሁም በሐኪም ወረዳ አካባቢ እየተከናወኑ የሚገኙ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችም ተጎብኝተዋል።
የተቀናጀ የሐኪም አካባቢ የልማት ፕሮጀክቶችም የሸዋልኢድን በዓል ምክንያት በማድረግ በቀጣይ ሣምንት የክልሉና የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት እንደሚመረቁ ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡