Fana: At a Speed of Life!

በወንዝ ዳር የሚከናወኑ የደጋፊ ግንብ ሥራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች እየተሠሩ የሚገኙ የወንዝ ዳር ደጋፊ ግንቦች ሥራ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡

በከተማዋ በመጪው ክረምት ሊከሰት የሚችልን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል በስምንት ቦታዎች የወንዝ ዳርቻ ደጋፊ ግንቦች ግንባታ እየተከናወነ ነው፡፡

ግንባታው እየተከናወነ ከሚገኝባቸው አካባቢዎች÷ ላምበረት መናኸሪያ ጀርባ፣ ጎፋ ካምፕ አካባቢ፣ ልደታ ወረዳ 5 43 የወጣቶች መዝናኛ ክበብ አካባቢ፣ ቦሌ ወረዳ 3 እና ወረዳ 10 ይጠቀሳሉ፡፡

ከላይ በስም በተጠቀሱት ቦታዎች ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባደረገው ቅኝት በወንዞቹ ጥግ ላይ ደጋፊ ግንብ በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተገነባ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

የደጋፊ ግንብ ግንባታ ሥራ መጀመሩ በመጪው ክረምት ሊከሰት የሚችልን የጎርፍ አደጋ ስጋት እንደሚቀንስላቸው የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የግንባታ ሥራውም በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ጠይቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እንዳሻው ከተማ÷ አፋጣኝ እልባት የሚያስፈልጋቸው የወንዞች ዳርቻ በጥናት መለየቱን ተናግዋል፡፡

ለዚህም ከ100 ሚሊየን ብር በመመደብ 15 የጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራትን በማሳተፍ ወደ ግንባታ መግባታቸውን ነው የገለጹት፡፡

የወንዝ ዳር ደጋፊ ግንብ ግንባታውን ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የግንባታ ጥራቱን በሚመለከትም በባለድርሻ አካላት ክትትል እንደሚደረግ ነው ያመላከቱት፡፡

በታሪክ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.