አስተዳደሩ ለሥራ ዕድ ፈጠራ በትኩረት ይሠራል- ከንቲባ አዳነች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሥራ ዕድል ፈጠራ በትኩረት እደሚሠራ የአስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ “ምክንያታዊ ወጣት ለአዲስ አበባ ብልጽግና” በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ 16 ሺህ ከሚሆኑ የከተማዋ ወጣቶች ጋር በሚሊኒየም አዳራሽ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
የመዲናዋ ወጣቶች ትልቅ ተስፋ ባላት ከተማ መኖራቸውን ተረድተው ከመለያየት ይልቅ ወንድማማችነትን በማጠንከር ሕይወታቸውን መቀየር በሚችሉ ሥራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ከንቲባዋ ጠይቀዋል፡፡
እኛም ሳንደክም የገባነውን ቃል ጠብቀን ያለረፍት እንሠራለን ብለዋል፡፡
ወጣቶቹ ጥያቄያቸውን ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ከለውጡ ወዲህ የተሠሩ ሥራዎች የሕብረተሰቡን የኑሮ ጫና በማቃለል ረገድ የተጫወቱትን ሚና እንደሚገነዘቡ ነግረውናል ብለዋል ከንቲባዋ፡፡
ወጣቶቹ ያነሱት የሥራ ዕድል ፈጠራ ተገቢ እና ወቅታዊ መሆኑን ገልጸው÷ በየደረጃው አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጠው እንሠራለን ነው ያሉት፡፡
70/30 የመኖሪያ ቤት ግንባታ በከተማችን ያለውን የቤት አቅርቦት እጥረት ከመቅረፍ ባሻገር 210 ሺህ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጠርም አመላክተዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!