Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ እና ሐረር የሚገኙ የተለያየ ሃይማኖት ተከታዮች የዒድ ሰላት የሚሰገድበትን ስፍራ አጸዱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ እና ሐረር ከተሞች የሚገኙ የተለያየ ሃይማኖት ተከታዮች የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የዒድ ሰላት የሚሰገድበትን ሥፍራ አጸዱ፡፡

የአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያን በማጽዳት ሥነ ስርዓቱ ላይ የሃይማኖት መሪዎች፣ አባ ገዳዎች፣ የተለያዩ እምነት ተከታዮች እና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃለፊዎች ተሳትፈዋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ያስሚን ወሃብረቢ እንደገለጹት÷ የዒድ ሰላት የሚሰገድበት ቦታን በሕብረት ማጽዳት የኢትዮጵያውያን አንድነት የጸና መሆኑን ማሳያ ነው።

በተመሳሳይ በሐረር ከተማ በተከናወነው የዒድ ሰላት የሚሰገድበትን ሥፍራ የማጽዳት ሥነ ስርዓት ላይ የተለያየ ሃይማኖት ተከታዮች፣ አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች የዒድ ሰላት መስገጃ ስፍራን ያለ ልዩነት ማጽዳታችን የአንድነታችን ማሳያ ነው ብለዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.