የሀገር ውስጥ ዜና

መንግስት በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታወቀ

By ዮሐንስ ደርበው

April 20, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤፌዴሪ መንግሥት በሱዳን ባለው ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋናው መስሪያ ቤት እና ካርቱም በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ አማካኝነት የኢትዮጵያውያንን ደኅንነት ለመጠበቅ እየሠራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና አጎራባች ክልሎች አባል የሆኑበት ግብረ ኃይል በሀገር አቀፍ ደረጃ መቋቋሙም ነው የተመለከተው፡፡

አስፈላጊ መረጃዎችን በቀጣይ እንደሚያሳውቅም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የገለጸው፡፡