የሀገር ውስጥ ዜና

ለ5 የንግድ የቴሊቪዥን ጣቢያዎች የስርጭት ፈቃድ እንዲሰጥ ተወሰነ

By ዮሐንስ ደርበው

April 20, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስት የንግድ የሳተላይት ቴሌቪዥን ብሮድካስት አገልግሎት ጣቢያዎች ፈቃድ እዲሰጣቸው መወሰኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ፈቃድ የሚሰጣቸውም የፋይናንስ አቅምና ምንጫቸው ስራውን ለማስኬድ አስተማማኝ መሆኑ ታምኖበት ነው ብሏል ባለስልጣኑ፡፡

አገልግሎቱን ለመስጠት ድርጅታዊ ብቃት ያላቸው በመሆኑ እና በፕሮጀክት ሠነዳቸው ያቀረቧቸው መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂዎች አገልግሎቱን ለመስጠት ብቃት ያላቸው ስለመሆኑ ተጣርቶ ውሳኔ ላይ መደረሱ ተገልጿል፡፡

የንግድ ቴሌቪዥን ፈቃድ ለማግኘት የቀረቡ አመልካቾችም በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በመቅረብ ውል እንዲዋዋሉና ከዛሬ ጀምሮ ፈቃዳቸውን መውሰድ እንደሚችሉ ባለስልጣኑ አስታውቋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!