Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ54 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ54 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለፀ፡፡

የኦሮሚያ ልማትና ፕላን ኮሚሽን እና የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮን ጨምሮ የ11 ሴክተሮች የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም እየተገመገመ ነው፡፡

በዚህ ወቅት የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ መስከረም ደበበ እንደተናገሩት÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 71 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 54 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል።

አፈጻጸሙ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ16 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ብልጫ አለውም ተብሏል ።

በውይይት መድረኩ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲን ጨምሮ የዘርፍ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.