Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) የትጥቅ ትግሉን በመተው ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለማካሄድ ጋምቤላ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ብሎ የሚጠራው ቡድን የትጥቅ ትግሉን በመተው ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለማካሄድ የቡድኑን አባላቱን በመያዝ ጋምቤላ ገብቷል።
 
ታጣቂ ቡድኑ እና የጋምቤላ ክልል መንግሥት በደቡብ ሱዳን ጁባ እና በአዲስ አበባ ከተማ ባደረጉት የሰላም ውይይት መሠረት ነው ወደ ክልሉ የተመለሱት፡፡
 
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እንዳሉት÷በደቡብ ሱዳን ጁባ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገው የጋራ ውይይት ታጣቂ ቡድኑ በሰላም ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
 
በስምምነቱ መሰረት የቡድኑ አባላት ትጥቃቸውን በሰላማዊ መንገድ ለክልሉ መንግስት ማስረከባቸውን ገልጸው ÷ለታጣቂ ቡድኖቹ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተሐድሶ ስልጠና እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
 
የተሐድሶ ስልጠናው ወደ ሰላማዊ የልማት እንቅስቃሴ ለመግባት እንደሚያግዝ የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ቡድኑ ስልጠናውን ወስደው ሲያጠናቅቁ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች እንዲሰማሩ የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ጠቁመዋል።
 
የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ሊቀመንበር አቶ ጋትሉዋክ ቡም በበኩላቸው÷ 195 የሚሆኑ የቡድኑ አባላት በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ጋምቤላ መግባታቸውን አስረድተዋል።
 
የትጥቅ ትግል አዋጭ የመታገያ ስልት ባለመሆኑ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለማድረግ የጋራ ውሳኔ ላይ እንደደረሱ መናገራቸውን የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመላክታል፡፡
 
#Ethiopia
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.