Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማዋ አመራሮች ከመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዑካን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ ባለፈው ጦርነት በመቀሌ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና፣ ትምህርትና የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶችን ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ምክክሩ የሕዝብ ለሕዝብ የህትማማችነት ትስስር መፍጠር እና በመዲናዋ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ልምድ በመቅሰም በመቀሌ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም ተጠቁሟል፡፡

በመድረኩ በጦርነቱ ወቅት በርካታ መሠረተ ልማቶችና ተቋማት መውደማቸው የተገለጸ ሲሆን÷ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን ለመደገፍ ለሚደረገው ጥረት  አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

ከተማ አስተዳደሩም ማህበረሰቡን በማስተባበርና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮችን በመለየት የቁሳቁስ፣ የባለሙያ እና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ከንቲባ አዳነች ቃል ገብተዋል።

በውይይቱም ከንቲባ አዳነችና አመራሮች፣ የመቀሌ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኤልያስ ካሳይን ጨምሮ ሌሎች የከተማዋ ጊዜያዊ አስተዳደረ አባላት ተሳትፈዋል።

 

 

በሳሙኤል ወርቃየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.