የሀገር ውስጥ ዜና

በምስራቅ ኢትዮጵያ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል መስተካከሉ ተገለጸ

By Shambel Mihret

April 20, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ በተፈፀመ ስርቆት ኃይል የተቋረጠበት የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢ በአማራጭ መስመር ኃይል አግኝቷል።

ኃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች ከቆቃ በአማራጭ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ የተደረገው ጥረት ውጤት በማስገኘቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞችና ጅቡቲ ኃይል ማግኘት ችለዋል።

ከአዋሽ ወደ ድሬዳዋ በተዘረጋው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ ሁርሶ አካባቢ በተፈፀመ ስርቆት ምሽቱን በምስራቅ ኢትዮጵያ ትልልቅ ከተሞችና አካባቢያቸው ሙሉ በሙሉ ኃይል ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ም ብለዋል፡፡