ዓለምአቀፋዊ ዜና

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በሱዳን ጉዳይ ላይ አስቸኳይ የሚኒስትሮች ስብሰባ አካሄደ

By Shambel Mihret

April 20, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በሱዳን ጉዳይ ላይ አስቸኳይ የሚኒስትሮች ስብሰባ ማካሄዱን የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሐመት ገለጹ።

በቴሌኮንፈረንስ በተካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው ላይ የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት /ኢጋድ/ ዋና ጸሐፊ  ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) መሳተፋቸው ተገልጿል።

የዓረብ ሊግ ሀገራት፣ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የሱዳን አጎራባች ሀገራት፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ኳታር እና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶችም በስብሰባው ላይ ተካፍለዋል።

የስብሰባው ተሳታፊዎች የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በሀገሪቱ አስቸኳይ የሰብአዊ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና በጦርነት ምክንያት መንቀሳቀስ ያልቻሉ ዜጎች አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያገኙ መጠየቃቸውን ስብሰባውን በሊቀመንበርነት የመሩት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሐመት ገልጸዋል።