የዒድ አልፈጥር በዓል በመዲናዋ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2015 ዓ.ም የዒድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በአዲስ አበባ በድምቀት ተከብሯል፡፡
የዒድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ እና በጉጉት የሚጠበቅ በዓል ነው፡፡
የዘንድሮው 1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓልም በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ነው በደመቀ መልኩ የተከበረው፡፡
በዓሉ በአዲስ አበባም በድምቀት እየተከበረ ሲሆን በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝተው የሶላት ስነ-ስርዓት አካሂደዋል፡፡ .