Fana: At a Speed of Life!

የኢድ ሶላት ስነ-ስርዓት በሰላም ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ1 ሺህ 444ኛው የኢድ አልፈጥር  በዓል የኢድ ሶላት ስነ ስርዓት በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሐይል አስታወቀ።

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የኢድ አልፈጥር በዓል የሶላት ስነ ስርዓት በርካታ ህዝበ ሙስሊም በተገኘበት በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ተካሂዷል።

ከንጋት ጀምሮም ወደ ሶላቱ ቦታ በሚደረግ ጉዞም ሆነ የሶላት ስነስርአቱ በሚካሄድበት ወቅት አንዳችም በዓሉን የሚያውክ ሁኔታ እንዳይፈጠርና የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም የፀጥታ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት መወጣታቸው ተመላክቷል፡፡

በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችም ከዚህ ቀደም ሲያደርጉት እንደነበረው የማስተባበሩን ሚና በመወጣት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቻቸው ነው የተገለፀው፡፡

በዚህም የአዲስ አበባ ነዋሪን ጨምሮ የሶላት ስነ ስርአቱ በሚካሄድበት ስፍራ በመገኘት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ድርሻቸውን ለተወጡ ሁሉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሐይል ምስጋና አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.