Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በቢሾፍቱ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቢሾፍቱ ከተማ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቢሾፍቱ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የከተማ ግብርና ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በዘርፉ የተሰማሩ የከተማዋ ነዋሪዎችም ባለን ትንሽ መሬት ላይ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በመስራታችን ተጠቃሚ ሆነናል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ህዝቡ በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም መስራት ከቻለ ባአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችል ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡

በጉብኝቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.