ቢዝነስ

በኦሮሚያ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ ይከናወናል

By Alemayehu Geremew

April 22, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንደሚከናወን የክልሉ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በኤሌክትሮኒክስ የሚከነወነው የነዳጅ ግዥና ሽያጭ የተሳለጠ እንዲሆንም የሚመለከታቸው አካላት ከወዲሁ ዝግጁ እንዲሆኑ ሲል ቢሮው አሳስቧል፡፡

በሌላ በኩል እንደ አቢሲያ ካርድ ኩፖን እና ሌሎች የግብይት መፈጸሚያ ዘዴዎች ሲጠቀሙ የነበሩ ተቋማት እስከያዝነው በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ ብቻ መጠቀም እንደሚችሉ ነው የተገለጸው፡፡

ኔትወርክ በሌለበት አካባቢም ሲ ቢ ኢ ብር በመጠቀም የነዳጅ ግብይት መፈጸም እንዲቻል ከቴሌ ጋር ስምምነት ላይ ተደርሶ መተግበሪያው መበልጸጉን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡