የሀገር ውስጥ ዜና

ታዋቂው የአፋን ኦሮሞ ድምፃዊ ዘሪሁን ወዳጆ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

By Melaku Gedif

April 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዋቂው የአፋን ኦሮሞ ድምፃዊ ዘሪሁን ወዳጆ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ድምፃዊው ለረዥም ጊዜ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቷል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በድምፃዊው ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በድምፃዊው ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ፥ ለቤተሰቦቹ እና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።