Fana: At a Speed of Life!

አትሌት መገርቱ ዓለሙ እና ታምራት ቶላ በለንደን ማራቶን 2ኛ እና 3ኛ ወጡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሔደው የለንደን 2023 ማራቶን ከሴቶች አትሌት መገርቱ ዓለሙ 2ኛ እንዲሁም ከወንዶች አትሌት ታምራት ቶላ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቁ፡፡

በተጨማሪም በወንዶች ልዑል ገብረ ሥላሴ 4ኛ እና ሰይፉ ቱራ 5ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡

ዛሬ የተካሄደውን የማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት ሲፈን ሀሰን አሸንፋለች፡፡

በመጀመሪያ የማራቶን ተሳትፎዋ ነው የለንደን ማራቶንን ማሸነፍ የቻለችው፡፡

አትሌት ሲፈን በትውልድ ኢትዮጵያዊ ስትሆን ለኔዘርላንድ እንደምትሮጥ ይታወቃል፡፡

እንዲሁም ኬንያዊቷ አትሌት ፔሬስ ጄፕቺርቺር ሦስተኛ ደረጃ ወጥታለች፡፡

በተመሳሳይ በወንዶች የተካሄደውን የማራቶን ውድድር ኬንያዊው አትሌት ኬልቪስ ኪፕተም አሸንፏል፡፡

አትሌት ኬልቪስ ኪፕተም 2 ሰዓት ከ1 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ በመግባት የዓለም ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግቧል፡፡

በሌላ በኩል በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 30ኛው የኬፕ ታውን የሴቶች የ10ኪሎ ሜትር የጎዳ ላይ ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ህያነ ለማ አሸነፍለች፡፡

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሰላም ገብሬ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.