Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን ለችግሮቻቸው በጥበብ እልባት ከማምጣት አንፃር የከፍተኛ ልምድ ባለቤት ናቸው – ሙሳ ፋኪ መሃማት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን ለችግሮቻቸው በጥበብ እልባት ከማምጣት አንፃር የከፍተኛ ልምድ ባለቤት ናቸው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ከሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት ተናገሩ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ወዳጅነት አደባባይ ‘ጦርነት ይብቃ፤ ሰላም እናጽና’ በሚል መሪ ሐሳብ የምስጋና እና የዕውቅና ሥነ ስርዓት ተካሒዷል፡፡

በሥነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ህብረት ከሚሽን ሊቀ መንበር÷ በክርስትናና በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ታላቅ ስፍራ ባላቸው በትንሳኤ እና በዒድ አልፈጥር በዓላት ማግስት ይህን ለመሰለ የሰላም ጉዳይ መሰባሰባችን ትልቅ ትርጉም አለው ብለዋል፡፡

አፍሪካውያን ከነበረው ክስተት በሁለት መንገድ ተምረናል ያሉት ሊቀመንበሩ÷ ከጦርነቱ ጥፋቱን ከስምምነቱ ደግሞ መፍትሄ መኖሩን ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን የጦርነትን አስከፊነት እና የሰላምን ጥቅም በሚገባ ያውቁታል ያሉት ሙሳ ፋኪ መሃማት ለችግሮቻቸው በጥበብ እልባት ከማምጣት አንፃርም የከፍተኛ ልምድ ባለቤት ናቸው ነው ያሉት፡፡

ለዚህም ያላቸው የትብብር ጥንካሬና የአመራር ብቃት ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ አህጉር ከመሰል ግጭቶች ልትፀዳ ይገባል ያሉት ሙሳ ፋኪ÷ ሱዳናውያንም ከዚህ ትልቅ ትምህርት በመውሰድ ግጭትን በማስወገድ ችግሮቻቸውን በሰከነ መንገድ ሊፈቱ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.