Fana: At a Speed of Life!

ስምምነቱ በተያዘለት ዕቅድ እየተፈጸመ ነው – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመውን ስምምነት በተያዘለት ጊዜ እየተፈጸመ መሆኑን ተናገሩ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ወዳጅነት አደባባይ ‘ጦርነት ይብቃ፤ ሰላም እናጽና’ በሚል መሪ ሐሳብ የምስጋና እና የዕውቅና ሥነ ስርዓት ተካሒዷል፡፡

ቀሪውንም ያለምንም ማመንታት መፈጸም እንደሚገባ ገለጹ፡፡

ከአውዳሚው ጦርነት ወደ ሰላማዊ አውድ ለመምጣት ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ግጭቱ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ማሕበራዊ ጉዳት ማድረሱንም አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ እፎይታ ያስፈልገዋል ያሉት አቶ ደመቀ÷ የተለያየ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው አካላት በሚጠምቁት ችግር በመነዳት ወዳልተገባ ግጭት ውስጥ በመግባት ውድ ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን ብሎም ህይወታቸውን እንዳይገብሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነትም ሳይሸራረፍ በሚገባ እንዲተገበር መንግስት እያደረገ ያለውን ያላሰለሰ ጥረት በማጠናከር ሰላምን የማጽናት ሥራው እንደሚቀጥልም ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልፀዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.