የሀገር ውስጥ ዜና

ከሸኔ ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ ይጀመራል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

By ዮሐንስ ደርበው

April 24, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሸኔ ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ፡፡

የወለጋ ሕዝብ እፎይ እንዲል ሁሉም ወገን የበኩሉን እንዲያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሌላ በኩል በቀጣዩ ሣምንት በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት የተመራ ልዑክ ወደ መቀሌ እንደሚያቀና ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገለጹት፡፡

ልዑኩ የሁሉንም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ያካተተ እንደሚሆን ነው የተናገሩት፡፡

ኢትዮጵያን እርዳታ ወደ ሱዳን ለመላክ ዝግጅት ስለማደረጉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይፋ አድርገዋል።

በዚህ የዕርዳታ ማዕቀፍ 50 ሺህ ኩንታል ስንዴ ወደ ሱዳን እንደሚላክ ነው ያስታወቁት።

የሱዳን ኃይሎች ለሰላማዊ አማራጭ ቅድሚያ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!