Fana: At a Speed of Life!

2 ዓመት ከመዋጋት 20 ዓመት መወያየት ይሻላል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠብ አቁሞ ሰላም ለመፍጠር በቂ ያልሆነ ምክንያት እና ትክክለኛ ያልሆነ ጊዜ የለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ወዳጅነት አደባባይ ‘ጦርነት ይብቃ፤ ሰላም እናጽና’ በሚል መሪ ሐሳብ የምስጋና እና የዕውቅና ሥነ ስርዓት ተካሒዷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚሁ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ይህንን ቀንን እንድናይ ያደረገንን ፈጣሪ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያመሰግን ከአደራ ጭምር አሳስባለሁ ብለዋል፡፡

ጠብ አቁሞ ሰላም ለመፍጠር በቂ ያልሆነ ምክንያት ትክክለኛ ያልሆነ ጊዜ የለም ነው ያሉት በንግግራቸው፡፡
ዛሬ እየሆነ ያለው የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ማብሰሪያ ዕለት ነው ብለዋል፡፡

“ፍቅር ይገነባል፣ ያሳስባል፣ ያስቃል፤ ጦርነት ግን፥ ያወድማል፣ ይገድላል፤ ሰላም ያለማል፣ ያበለጽጋል፤ ጦርነት ግን ጨለማ እና ክፉ ነው” ሲሉ አብራርተዋል፡፡

ሰላም ብርሃን ነው፤ የነገር ሁሉ መጀመሪያም ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

“ለዚህ ሰላም እድንበቃ ላደረጋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡

“ኢትዮጵያውያን በቂ የጦርነት ታሪክ አለን፤ በቂ የሰላም ታሪክ ግን የለንም” ነው ያሉት፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.