Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ የማህፀን በር ካንሰርና የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ የማህፀን በር ካንሰርና የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶች ዘመቻ ከነገ ጀምሮ ሊካሄድ መሆኑን የከተማው ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የክትባት ዘመቻው ከሚያዝያ 17 እስከ 21 ቀን 2015ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ አስታውቀዋል።

ቢሮው የተለያዩ የክትባት ዘመቻዎችን በማዘጋጀት ጭምር የክትባት ሽፋንን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ነው የገለጹት።

በእነዚህ ሁለት ዘመቻዎችም በአጠቃላይ ከ71 ሺህ በላይ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ተደራሽ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚሁ መሰረት ከሚያዝያ 17 ጀምሮ ለ4 ቀናት በሚቆየ የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ 9ሺህ 700 በላይ የሚሆኑ እድሜያቸው 14 ዓመት የሆናቸውን ሴት ልጆች ለመከተብ ዕቅድ ስለመያዙ ተናግረዋል፡፡

ክትባቱ በትምህርት ቤቶችና በጤና ተቋማት የሚሰጥ ሲሆን ፥ ለስኬታማነቱ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

በተጨማሪም የ4ተኛ ዙር የኮቪድ- 19 መከላከያ ክትባት ከሚያዝያ 21 ጀምሮ እንደሚካሄድ ሃላፊዋ ጠቁመው በዚህም ከ64 ሺህ በላይ ሰዎችን ለመከተብ መታቀዱን ገልፀዋል፡፡

ከአሁን በፊት በመደበኛነት በተሰጠው ክትባት ከ200 ሺህ በላይ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ክትባቱን መውሰዳቸው ታውቋል፡፡

በኢዮናዳብ አንዱዓለም

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.