የሀገር ውስጥ ዜና

የፀጥታ ሁኔታን ለማጠናከር የጸጥታ አካላትን ቅንጅታዊ ስራ ያስፈልጋል – ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ

By Meseret Awoke

April 24, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተሻሻለ የመጣውን የፀጥታ ሁኔታ አጠንክሮ ለማስቀጠል የጸጥታ አካላትን ቅንጅታዊ ስራ እንደሚያስፈልግ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለጹ፡፡

14ኛው የፖሊስ ኮሚሽነሮች ጉባዔ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ÷ የሀገራችን የፀጥታ ሁኔታ እየተሻሻለ በመሆኑ ይህንኑን ይበልጥ ለማጠናከርም ተከታታይና ቀጣይነት ያለው ቅንጅታዊ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ፡፡

የፖሊስ አገልግሎትን ለማሻሻልና የመፈጸም አቅምን ለማሳደግ በየደረጃው ስልጠና እየተሰጠ መሆኑንም አንስተዋል።

በጉባዔው የሚተላለፉ ውሳኔዎች የፖሊስን አገልግሎት በሚገባ አሻሽለው ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል እንደሚሆን ይጠበቃልም ብለዋል።

ጉባዔው የፌደራል፣ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነሮች ተገቢውን ውሳኔ የሚሰጡበት እንደሚሆን መገለጹን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!