Fana: At a Speed of Life!

የቻይና አፍሪካ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ወደ ተግባር መቀየር የሚያስችል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና አፍሪካ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) የተመራ የልዑካን ቡድን በቻይና የሥራ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቻይና አፍሪካ የትብብር ማዕቀፍ አንዱ አካል የሆነውን ስምምነት ከዚህ ቀደም የተፈራረመ ሲሆን÷ ዛሬ በቻይና ስምምነቱን ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

በውይይቱ የቴክኒክና ሙያ ሥርዓተ-ትምህርት ቀረፃ፣ የተቋማት አቅም ግንባታ፣ የማሰልጠኛ መሳሪያዎች ድጋፍ እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ዲጂታላይዝድ ከማድረግ አኳያ እና ሌሎች በስምምነቱ የተመላከቱ ጉዳዮችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት ተነስተዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በቆይታው ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች ምልመላ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ከኢንተርፕሪነርሺፕ አኳያ ልምድ መቅሰም የሚያስችልና ከኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር ትስስር የሚፈጥሩ የማሰልጠኛና የቴክኖሎጂ ተቋማትን እንደሚጎበኝም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.