Fana: At a Speed of Life!

የፋና ላምሮት የ3ኛው ዙር የባለተሰጥኦ ድምፃዊያን የፍፃሜ ውድድር አሸናፊ ታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፋና ላምሮት የባለተሰጥኦ ድምፃዊያን ውድድር በፋና ቴሌቪዥን በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
 
በውድድሩም ለመጨረሻው ዙር ያለፉ ድምፃዊያን ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።
 
አራቱ ተወዳዳሪዎችም በፋና ቴለቪዥን በቀጥታ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል በተመልካቾች የአጭር የፅሁፍ መልዕክት እና በዳኞች ውጤት ተሰጥቷቸዋል።
 
በዚህ ተመልካቾችና ዳኞች በሰጡት አጠቃላይ ውጤት ዮናታን ንብረት የፋና ላምሮት የ3ኛው ዙር የባለተሰጥኦ ድምፃዊያን የፍፃሜ ውድድር አሸናፊ ሆኗል።
 
አዲስአለም ሸምሱ ሁለተኛ ፣ ግዛቸው ሙላት ሶስተኛ እና አሸብር ፈለቀ አራተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።
 
በዚህም አንደኛ ደረጃን ይዞ ላጠናቀቀው 100 ሺህ ብር ፣ ለሁለተኛ ደረጃ 75 ሺህ ብር ፣ ለሶስተኛ እና ለአራተኛ በቅድም ተከተላቸው 50 ሺህ እና 25 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
 
ከዚህ ባለፈ አንደኛ ደረጃ ይዞ ላጠናቀቀው ዮናታን ንብረት ነጣላ ዜማ ከነክሊፑ እና ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ላጠናቀቀው አዲስአለም ሸምሱ ነጣለ ዜማ እንዲያዘጋጁ ቃል ተገብቶላቸዋል።
 
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም 3ኛው ዙር የባለተሰጥኦ ድምፃዊያን ውድድር ለዳኙት ዳኞች እና ለክብር እንግዳው ለሙዚቃ አቀናባሪው አበጋዝ ክብረወርቅ ስጦታ አበርክቷል።

 

 

በኤፍሬም ምትኩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.